• Support
  • Our Campus
  • Official Login
  • Privacy & Terms
  • FAQ

Our Campus

Hawassa Campus Location: Ethiopia, Sidama Region, Hawassa City around Godguada
Establishment Year: 2002
Dilla Campus Location: Ethiopia, South Region, Dilla around 01
Establishment Year: 2005
Wolaita Campus Location: Ethiopia, South Region, Wolaita around 03
Establishment Year: 2005

Official Login

Wolaita Sodo Login
Hawassa Login
Dilla Login

Privacy Policy & Terms

በ Infolink University College 🎓

📄 የSchool System አጠቃቀም መመሪያ እና የደህንነት መግለጫ ይህ መግለጫ የተማሪዎችን እና የመምህራንን መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም ሲስተሙን በአግባቡ ለመጠቀም እንዲረዳ የተዘጋጀ ነው።

1. ስለ አጠቃቀም (Terms of Service)

📝መለያ (Account): እያንዳንዱ ተማሪ እና መምህር በዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን መለያ (Username እና Password) ብቻ የመጠቀም ግዴታ አለበት። 📝ኃላፊነት: በመለያዎ ለሚከናወኑ ማናቸውም ተግባራት (ለምሳሌ፡ ውጤት ማየት፣ ትምህርታዊ ቁሳቁሶችን መጫን) እርስዎ ቀጥተኛ ኃላፊነት ይወስዳሉ። 📝የተከለከሉ ተግባራት: ሲስተሙን ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት፣ የሌሎችን መረጃ ለመሰርሰር (Hacking) መሞከር እና የሀሰት መረጃዎችን መጫን በጥብቅ የተከለከለ ነው።

2. ስለ ደህንነት (Security)>

📝የይለፍ ቃል ጥበቃ: የይለፍ ቃልዎን ለማንም አሳልፈው አይስጡ። በየጊዜው መቀየር እና ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም ይመከራል። 📝መውጫ (Logout): ሲስተሙን ተጠቅመው ሲጨርሱ ሁልጊዜ "Logout" ማድረጋቸውን ያረጋግጡ፤ በተለይም በጋራ ኮምፒውተሮች ላይ ሲጠቀሙ። 📝የጥቃት መከላከል: ሲስተሙ በዘመናዊ የኢንክሪፕሽን (Encryption) ቴክኖሎጂ የተጠበቀ ቢሆንም፣ ተጠቃሚዎች የራሳቸውን መሣሪያ ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው።

3. ስለ ምስጢራዊነት (Privacy Policy)

📝የመረጃ አሰባሰብ: ዩኒቨርሲቲው ለትምህርት ስራ አስፈላጊ የሆኑ የግል መረጃዎችን (ስም፣ ስልክ፣ የትምህርት ውጤት፣ የመለዮ ቁጥር) ብቻ ይሰበስባል። 📝የመረጃ አጠቃቀም: የተሰበሰቡ መረጃዎች ለትምህርት አስተዳደር፣ ለውጤት መግለጫ እና ለግንኙነት ተግባራት ብቻ ይውላሉ። 📝ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት: ማንኛውም የተማሪ ወይም የመምህር መረጃ ያለባለቤቱ ፈቃድ ወይም ያለ ህግ ትእዛዝ ለሶስተኛ ወገን (ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ላለ አካል) ተላልፎ አይሰጥም።

4. ስለ ሌሎች ድንጋጌዎች

📝የሲስተም መቋረጥ: ለጥገና ሲባል ሲስተሙ ለተወሰነ ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል፤ ይህም አስቀድሞ በዩኒቨርሲቲው በኩል የሚገለጽ ይሆናል። 📝ደንብ መጣስ: ከላይ የተጠቀሱትን ደንቦች መጣስ ከመለያ መታገድ እስከ ዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር እርምጃዎች ሊያደርስ ይችላል። 📝ማሳሰቢያ: ይህ ሲስተም የእርስዎን የትምህርት ጉዞ ለማቀላጠፍ የተዘጋጀ በመሆኑ፣ በታማኝነት እና በጥንቃቄ በመጠቀም ለተቋሙ እድገት የድርሻዎን ይወጡ። 📝ስለ ሲስተሙ አጠቃቀም ወይም ስለ መረጃዎ ደህንነት ተጨማሪ ጥያቄ ካለዎት የዩኒቨርሲቲውን የIT ክፍል ማነጋገር ይችላሉ።

ተዘውታሪ ጥያቄዎች (FAQ)

1. የተማሪ መታወቂያ (Student ID) እንዴት ማስገባት እችላለሁ?

📝የተማሪ መታወቂያ (Student ID) ሲያስገቡ በመታወቂያዎ ላይ የሚገኙትን ቁጥሮች ብቻ በመውሰድ መሆን አለበት። ለምሳሌ፦ የመታወቂያ ቁጥርዎ IWEITTS-1234-18 ከሆነ፣ የሚያስገቡት 1234-18 ብለው ነው።

2. የገጽ መግቢያ የጥበቃ ቃል (Password) ከየት ማግኘት እችላለሁ?

📝ለሁሉም ተማሪዎች መጀመሪያ የሚሰጥ መደበኛ የጥበቃ ቃል (Default Password) 994 ነው። 📝ማሳሰቢያ፦ ተማሪዎች ይህንን Password ለመጀመሪያ ጊዜ ብቻ በመጠቀም ከገቡ በኋላ፣ ወዲያውኑ ወደ ግል Password መቀየር ይኖርባቸዋል።

3. የጥበቃ ቃል (Password) ቢጠፋብኝ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

Password ከረሱ ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን በራሳቸው Reset ማድረግ የሚችሉበት ሲስተም ተዘርግቷል። 📝በመግቢያ ገጹ (Login Page) ላይ የሚገኘውን "Forgot Password" የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ። 📝ተማሪ ከሆኑ፦ የራስዎን Student ID ያስገቡ። 📝መምህር ከሆኑ፦ የራስዎን ስልክ ቁጥር ያስገቡ። 📝የማረጋገጫ ኮድ (OTP) በስልክዎ፣ በኢሜይልዎ ወይም በቴሌግራም ቦት ይላክልዎታል። ያንን ኮድ በማስገባት አዲስ Password መፍጠር ይችላሉ።

4. የአካውንቴን ደህንነት እንዴት መጠበቅ እችላለሁ?

📝የአካውንትዎን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚከተለውን አማራጭ ይጠቀሙ፦ 📝ወደ አካውንትዎ በመግባት "Secure Login Setting" የሚለውን On ያድርጉ። 📝ይህንን ሲያደርጉ፣ ወደ አካውንትዎ በገቡ ቁጥር የማረጋገጫ ኮድ በኢሜይል/ስልክ/ቴሌግራም ይላክልዎታል። ኮዱን ሲያስገቡ ብቻ አካውንቱ ይከፈታል። 📝ጥቅሙ፦ ሌላ ሰው የእርስዎን Password ቢያውቅ እንኳ፣ የእርስዎ ስልክ ወይም ኢሜይል ሳይኖር ወደ አካውንቱ መግባት አይችልም።

የሚሰጡ አገልግሎቶች

🈶ለተማሪዎች፦ 📝ውጤት መመልከት፦ የክፍል እና የፈተና ውጤቶችን በማንኛውም ጊዜ ማየት። 📝የአየር ላይ ፈተና (Online Exam)፦ በሲስተሙ አማካኝነት ፈተናዎችን መውሰድ። 📝መረጃና የቤት ስራ፦ ከመምህራን የሚላኩ መረጃዎችን እና Assignment ማግኘት፣ እንዲሁም ከሰሩ በኋላ በዚያው Submit ማድረግ። 📝የጊዜ ሰሌዳ (Time Table)፦ የክፍል ክፍለ-ጊዜዎችን መከታተል። 📝Class Chat፦ እንደ ሶሻል ሚዲያ መረጃዎችን Post ማድረግ፣ Like/Share/Comment መስጠት እና ከጓደኞች ጋር በግል (Private Chat) መጻጻፍ (ቪዲዮ እና ፋይሎችን ጨምሮ)። 📝ክፍያ መፈጸም፦ ወርሃዊ ክፍያዎችን በቀጥታ መክፈል እና ደረሰኝ መቀበል። 📝ዲጂታል ቤተ-መጽሐፍት (Digital Library)፦ የትምህርት መርጃ ቪዲዮዎችን፣ PDF፣ ምስሎችን እና ጥያቄና መልሶችን ማግኘት። 📝ቀጥታ ውይይት (Conference)፦ በመምህራንና በተማሪዎች መካከል የሚደረጉ የቀጥታ የቪዲዮ እና የድምጽ ውይይቶች ላይ መሳተፍ። 📝ቅሬታና ጥቆማ፦ ማንኛውንም ጥያቄ ወይም አስተያየት በቀጥታ ለመምህራን ወይም ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር መላክ። 🈶ለመምህራን፦ 📝የተማሪዎች ክትትል (Attendance)፦ የተማሪዎችን የቀን ተቀን መገኘት መመዝገብ። 📝ውጤት መያዝ፦ የተማሪዎችን ውጤት መመዝገብና ዝርዝራቸውን መመልከት። 📝መረጃ ማጋራት፦ Assignment እና ልዩ ልዩ መረጃዎችን ለተማሪዎች Post ማድረግ። 📝ማረምና መገምገም፦ ተማሪዎች የላኩትን Assignment አይቶ ውጤት መስጠት። 📝ፈተና ማዘጋጀት፦ ለተማሪዎች የኦንላይን ፈተናዎችን ማዘጋጀትና ማስፈተን። 👉ጠቃሚ ማሳሰቢያ፦ ማንኛውም አይነት የቴክኒክ ችግር ካጋጠመዎት የትምህርት ቤቱን የአስተዳደር ቢሮ ያነጋግሩ።

Login

🎓የተማሪ ማንነት ማረጋገጫ